Friday, June 13, 2014

በግንደ በረት በተማሪዎች እና በክልሉ ፖሊስ መካከል ከፍተኛ የሆነ ግጭት ተከሰተ

federal police
 በምእራብ ሸዋ ዞን በኦሮሚያ ክልል በግንደበረት ወረዳ በተማሪዎች እና በወያኔ የፖሊስ ሃይሎች መካከል በተከሰተ ግጭት አንድ ተማሪ ሞቶ አራት መቁሰላቸውን የአከባቢው ምንጮች ገልጸዋል።
ከትላንትና ጀምሮ ሲንከባለል የመጣው ግጭት ከዚህ ቀደም በኦሮምያ ክልል ውስጥ ከተነሱ የተማሪዎች አመጽ ጋር ተያያዥነት ያለው እና ጥያቂውም የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እና የሞቱ የኦሮሞ ተማሪዎች ጋር የተያያዘ ሲሆን ዛሬ በቀጠለው ተቃውሞ ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች እና የወረዳው ነዋሪ በጋራ ሰልፍ በመውጣት ቁጣቸውን የገለጹ ሲሆን አስተዳደሩ ድረስ በመሄድ ድምጻቸውን ሲያሰሙ የፌዴራል ፖሊስ በመምጣት የበተናቸው ቢሆንም ቀኑን ሙሉ በከተማው ከባድ ረብሻ እንደነበር እና ከቆሰሉ ተማሪዎቹም አንዱ መሞቱን የወረዳው ነዋሪዎች ተናግረዋል ሲሉ ምንጮቹ ጠቁመዋል።
በነገው እለት የ12ኛ ክፍል መሰናዶ ፈትና ከወሰደ በኋላ የተገደለውን ተማሪ ለመቅበር ይወጣል የተባለው ሕዝብ ተቃውሞ እንዳያሰማ የወረዳው እና የከተማው ባለስልጣናት በመስጋት ፖሊሶች ያሰፈሩ ሲሆን ሕዝቡ ቁጣው እንዳልበረደ እና በስፋት ተቃውሞው እንደሚቀጥሉ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
june 13,2014 Ze-Habesha

No comments:

Post a Comment