Thursday, September 19, 2013

ሀበሻም ሆነ የሀበሻ አመለካከት ወይም አሰተሳሰብ ያለዉ፦ ሁለቱም የኦሮሞ የነፃነት ትግል ፀር ናቸዉ

ወደ ጽሁፌ ዋናዉ ይዘት ከመግባቴ በፊት አሰቀድሜ አንድ ነገር ግልፅ ማድረግ እፈልጋለሁ። ይኸዉም ሀበሻ (አብሲንያ) የኦሮሞ የነፃነት ትግል ፀር ነዉ ስል ሰላማዊዉን ያአማራም ሆነ የትገሬ ብሔር ሕዝቦችን በጅምላ ባንድ አይን ማየቴ ሳይሆን ስለ ኦሮሞ የነፃነት ትግል ፀር በማነሳበት ጊዜ በይበልጥ የማተኩረዉ ከነዚሁ ብሔሮች ዉሰጥ በወጡት አሮጌ (የአማራ) እና አዲሱ (የትግሬ) ነፍጠኞች ላይ ነዉ። የኦሮሞ የነፃነት ትግል ፀር የሆኑትም እነዚሁ ሐይሎችና የነሱን አሰተሳሰብ ወይም አመለካከት ተከትለዉ የሚሄዱ ጀሌዎቻቸዉ ናቸዉ። የነሱ አሰተሳሰብ ወይም አመለካከት ያላቸዉ ጃሌዎች ስል ምን ማለቴ ነዉ? እነዚህ ጀሌዎች የሀበሻን (ነፍጠኛን) አሰተሳሰብ የሚያንፀባርቁት በተለያዩ መንገዶች ሲሆኑ ከነዚህ መነገዶች ዉሰጥ አንዳንዶቹን ባጭሩ ለማብራራት እሞከራለሁ።
አንደኛ መንገድ ከሀበሻ እምነት ጋር በተለይም ከኦርቶዶክስ ሃይማኖት ጋር ትስስር ስለኣላቸዉ በዚህ በኩል ደግሞ በሚነገራቸዉ ወይም በሚሰበካቸዉ የኢትዮጵያዊነት ስሜት የተነሳ ማንነታቸዉን እነዲረሱ ወይንም ጥያቄ ዉስጥ እንዲያሰገቡ ይደረጋሉ። የማንነት ቀዉስ (identity crisis) ያላቸዉ እነዚሁ ሰዎች ዋንኛዉ ምክንያት የሚመነጨዉ ከዚህ ነዉ ማለት ይቻላል። ለዚህም ነዉ እነዚህ ሰዎች ማንነታቸዉን (ሆነዉ የተፈጠሩትን) ትተዉ በሌላ መንገድ የተጫነባቸዉን ኢትዮጵያዊነትን የሚያሰቀድሙት።
ሁለተኛዉ መንገድ በጋብቻና በሌሎች መንገዶች ከሀበሻ ጋር መቀላቀል ነዉ። ሀበሾች በተለይም ነፍጠኞች የኦሮሞን የነፃነት ትግል፣ የኦሮሞን የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ባንድ መንገድ ብቻ ነዉ የሚያዩት። ይህም ጥዋትና ማታ እንደሚዘፍኑት የመገንጠል ጥያቄ ነዉ። ስለዚህ በጋብቻ ከነሱ ጋር የተቀላቀሉትን መሳሪያ በማድረግ፣ ነገ ኦሮሚያ ብትገነጠል በመሃል (ከሀበሾችና ኦሮሞ) የተወለዱት ወይም ሚወለዱት ልጆች ዕጣ ፋነታቸዉ ምን ይሆናል በማለት ከነሱ ጋር በጋብቻ የተቀላቀሉትን ኦሮሞዎች በፕሮፓጋንዳቸዉ በማደንቆር ለኦሮሞ የነፃነት ታጋዮች እንቅፋት እንድሆኑባቸዉ ያደርጔቸዋል። እነዚህም ኦሮሞዎች በዚሁ ፐሮፓጋንዳ በመታለል የሀበሾች ጀሌዎች እንድሆኑ ይደረጋሉ ማለት ነዉ።
ሦስተኛዉ መንገድ ደግሞ የፖለቲካ አስተሳሰብ ወይም አመለካከት (political ideology) ነዉ። ይህ ጉዳይ ሰፊ ትንታኔ የሚጠይቅ ስለሆነ ሌላ ጊዜ በሰፊዉ እመለስበታለሁ። ለዛሬ ግን አንዳንድ ነገሮችን ባጭሩ ለማንሳት እሞክራለሁ። የፖለቲካ አሰተሳሰብ ወይም አመለካከት ራሱ ከተለያየ አቅጣጫ ነዉ የሚመነጨዉ። ከነዚህ ዉሰጥ አንዱ በራስ አለመተማመን ነዉ። በራስ አለመተማመን ደግሞ በመጀመሪያ አንግበዉ የተነሱለትን ዓላማ ትተዉ ወደ ሌላ አቅጣጫ እንዲሄዱ ያደርጋል። የዓለምና የአካባቢ ሁኔታ መለወጥ፣እንደዚሁም ደግሞ የነፃነት ትግል መርዘም፣ በዚህም የተነሳ ትግዕስት ማጣት ወይም ተስፋ የመቁረጥ ሁኔታ ስለሚፈጠር የቆሙለትን ዓላማ ትተዉ በተቃራኒ መንገድ እንድሄዱ ያደርጋል ማለት ነዉ።
እንግዲህ የሀበሻ (የነፍጠኛ) አሰተሳሰብ ወይም አመለካከት ያላቸዉ ጃሌዎችን ባጭሩ ካብራራሁ በኋለ ወደ ዋናዉ የፅሁፌ ርዕስ በመመለስ፣ሀበሾችም ሆኑ ጀሌዎቻቸዉ እንዴት የኦሮሞ የነፃነት ትግል ፀር እንደሆኑ ከዚህ ቀጥዬ አንዳንድ ነገሮችን ለመጠቃቀስ እሞክራለሁ።
እንደሚታወሰዉ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኦሮሞነት (Oromummaa) ላይ የፀረ ማንነት ዘመቻ ስካሄድ ነበር። በኦሮሞነት ላይ የሚደረገዉ ዘመቻ የተጀመረዉ ዛሬ ባይሆንም ነገር ግን በይበልጥ ጎልቶ የታየዉና እንደ ቦምብ የፈነዳዉ በአልጃዝራ ቴሌቭዥን (Aljazeera TV) ላይ ከሶስት የኦሮሞ ታጋዮች ጋር ስለ ኦሮሞ ህዝብ ጉዳይ ዉይይት ከተካሄደ ወዲህ ነዉ። እነደምታወቀዉ በዚህ ጉዳይ ላይ በቀረበለት ጥያቄ መሠረት ወጣቱ የኦሮሞ ታጋይ ጀዋር መሃመድ ”I am Oromo First” ብሎ ከተናገረ በኋላ ይህ ጉዳይ ነፍጠኞችንና ጀሌዎቻቸዉን ከማስቆጣት አልፎ እንደ እብድ ዉሻ ስያደርጋቸዉ ነበር። ለምንድነዉ እነደዚያ የምያደርጋቸዉ ብለን ጥያቄ ብናነሳ፣ ለዚህ ጥያቄ መልስ የሚሆኑትን የተለያዩ ምክንያቶችን መጥቀስ ቢቻልም ትልቁና ዋንኛዉ ምክንያት ኦሮሞነት (Oromummaa) የኦሮሞ የነፃነት ትግል ሞተር (engine) ስለሆነ፣ ይህንን ትግል ለማዳከም በመጀመሪያ ኦሮሞነትን ማዳከም አስፈላጊ ስለምሆን ሀበሻና ጀሌዎቻቸዉ በ Oromummaa ላይ ዘመቻ ያካሂዳሉ። በነገራችን ላይ ለምሳሌ እንበልና ጀዋር መሃመድም ሆነ ሌላ ኦሮሞ ተነስቶ I am Wallaggaa Oromo… ወይም Arsii Oromoo… ወይም Baalee Oromoo… ወይም Boranaa Oromoo ወይም Shawaa Oromoo First ብሎ ቢናገር፣ ሀበሾች ከመቆጣት ይልቅ ወሰን የለሽ ደስታቸዉን እንደሚገልጹ አያጠያይቅም። ለምን ቢባል የኦሮሞ ሕዝብ በክልል፣ አካባቢና ሃይማኖት መለያየት ለነሱ ትልቁ ፍላጎትና ዓላማቸዉም ስለሆነ ነዉ። ለነሱ ራስ ምታትና ነቀርሳ የሚሆንባቸዉ የ Oromummaa ማደግና መጠናከር ነዉ። የ Oromummaa ማደግና መጠናከር የኦሮሞን አንድነትና ሀይል ያጠናክራል። የኦሮሞ አንድነት መጠናከር የነፃነት ትግሉን ያጠናክራል ማለት ነዉ።
አሮጌዉንና አዲሱን ነፍጠኞች አንድ የሚያደርጋቸዉ ጉዳይ ሁለቱም Oromummaa ን እንደ አንድ የጋራ ጠላታቸዉ ማየታቸዉ ነዉ። ይህንን የጋራ ጠላታቸዉን ለማጥፋት በሚያደርጉት ዘመቻ ላይ ሁለቱም ይደጋገፋሉ። ዛሬ ባገራችን ኦሮሚያ ዉስጥ በአዲሱ ነፍጠኞች (በወያኔዎች) የሚታሰሩ፣ የሚገደሉና ከሀገር የሚሰደዱት ኦሮሞዎች በ Oromummaa የበሰሉ የኦሮሞ ብሔረተኞች ናቸዉ። “ሊጣላ የመጣ ሰበብ አያጣ “ እንደሚባለዉ በኦነግነትና በአሸበርተኝነት ተወንጅለዉ ለእስራት፣ ለሞትና ለስደት ይዳረጋሉ እንጂ ትልቁ ምክንያት ግን በ Oromummaa ላይ የሚደረገዉ የማንነት የማጥፋት ዘመቻ ነዉ። በወጣት ጀዋር መሃመድና በወጣት አብዲ ፊጤ ላይ የተደረገዉ ዘመቻ በግልፅ የሚያሳየዉ እነዚህ ወጣት ታጋዮች የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባል ወይንም አሸባሪዎች ሆነዉ ሳይሆን ለማንነታቸዉ ለ Oromummaa ቅድሚያ በመስጠታቸዉ ብቻ ነዉ። ማንነታቸዉን ትተዉ ለምን ኢትዮጵያዊነትን አያስቀድሙም ነዉ።
በዚህች በደም በተገነባች ኢምፓየር ዉስጥ ይቅርና የሁሉም ሕዝቦች እኩልነት በተጠበቀበት ሀገር ዉሰጥ እነኳን ማንም ሰዉ ማንነቱን (ሆኖ የተፈጠረዉን) እኔ ……. ነኝ ብሎ ከመናገር ይልቅ ማንነቱን ( identity) ትቶ ለሌላ ነገር ቅድሚያ ይሰጣል ብሎ ማሰብ ከእዉነት መራቅ ይሆናል። ነፍጠኞችና ጃሌዎቻቸዉ አንድ የዘነጉት ነገር አለ። ዛሬ የኦሮሞ የነፃነት ትግል የተዳከመ ወይም የቀዘቀዘ መስሎ ቢታያቸዉም፣ አዲሱን የኦሮሞ ትዉልድ በተለይም የቁቤን ትዉልድ (Qbee generation) ይቅርና ያልነቃዉንም የኦሮሞ ሕዝብ በማታለል ኢትዮጵያዊነትን በነሱ ላይ በመጫን የፖለቲካ ዓላማቸዉን ከግብ ለማድረስ የሚያደርጉት ወቅት ማለፉን ነዉ። በነገራችን ላይ ባሁኑ ወቅት ያልነቃ የኦሮሞ ሕዝብ ስለሌለ ለአባባል ያህል ይህንን ሐረግ በመጥቀሴ ሕዝቤን ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ። ነፍጠኞችና ጃሌዎቻቸዉ ዛሬም ከ 22 ዓመታት በፊት በነበረዉ ጭነቅላታቸዉ ያስባሉ ብል ነገር ማጋነን አይሆንብኝም።
የአሮጌ ነፍጠኞች (የአማራ የገዥ ወገኖች) ትልቁ ዓላማቸዉ በዉድ የኦሮሞ ልጆች ደምና አጥንት የተገኘዉን ኦሮሚያን ከካርታ ላይ መፋቅና QUBEE ን ማጥፋት ነዉ። ባጠቃላይ ምኞትና ፍላጎታቸዉ የኦሮሞ የነፃነት ትግል እስከ ዛሬ ያስመዘገባቸዉን ድሎች ሁሉ ማጥፋት ነዉ። ይህንን ለማጥፋት ደግሞ የመጀመሪያ እርምጃ የኦሮሞን የብሔርተኝነት ስሜት መግደልና Oromummaa ን ማጥፋት ይሆናል። ለዚህም ነዉ ለምን ማንነታችሁን ትገልፃላችሁ፤ ለምን ማንነታችሁን ታስቀድማላችዉ እያሉ ዘመቻ የሚያካሄዱት። Oromummaa ን ማጥፋትና የኦሮሞን የብሔርተኝነት ስሜት መግደል ማለት ደግሞ የነፃነት ትግሉን ሞተር ማጥፋት ማለት ነዉ። ሞተሩ ከጠፋ ደግሞ የተጀመረዉ ትግል ጉዞዉን ቀጥሎ ከግብ መድረስ ስለማይችል የነሱ ፍላጎትና ዓላማ ተሳካላቸዉ ማለት ነዉ። ይሁን እንጂ ይህ የቀን ሕልማቸዉ መሆኑን መረዳት አለባቸዉ።
ወደ ፅሁፌ ማጠቃለያ ከመሄዴ በፊት የኦሮሞ የነፃነት ትግል ፀር ለሆኑት ሀይሎች ሁሉ የሚከተለዉን መልዕክት ማስተላለፍ እወዳለሁ።
በመጀመሪያ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ሆናችሁ ግን የሀበሻ ጃሌዎች ለሆናችሁ፦
በእምነት ወይም በሀይማኖት፣ በጋብቻ፣ በማሕበራዊ ኑሮና በፖለቲካ አመለካከት ከሀበሻ ጋር ትስስር የፈጠራችሁት ሁሉ የሰፊዉ የኦሮሞ ሕዝብ የወደፊት ዕጣዉ፣ የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን መብቱ በእናንቴ ጥቅማትቅም መወሰን እነደማይችል በመገንዘብ ከእናት፣ ከአባት፣ ከወንድምና እህቶቻችሁ ጎን በመቆም፤ የዛሬን ጥቅምን ሳይሆን የነገዉን የሕዝባችሁን ግብ በማየት የኦሮሞ የነፃነት ትግል ፀር ከመሆን ፋንታ የትግሉ አጋዥ እንድትሆኑ የትዉልድ ግዴታችሁን እነድትወጡ ጥሪ ላቀርብላችሁ እወዳለሁ።
የኦሮሞ የነፃነት ትግል ፀር ለሆኑ ሀይሎች፦
የኦሮሞ የነፃነት ትግል የፖለቲካን ስለጣን ለመያዝ የሚደረገዉ ትግል አይደለም። ስሙ እንደሚገልፀዉ ይህ ትግል የነፃነት ትግል ነዉ። የሚፈለገዉ ነፃነት እስከሚጎናፀፍ ድረስ የማይቆምና የሚቀጥል ትግል ነዉ። የሰፊዉ የኦሮሞ ሕዝብ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ትግል ነዉ። ይህ እስከሚረጋገጥ ድረስ ከትዉልድ ወደ ትዉልድ የሚተላለፍ ትግል ነዉ። በ 1991 የተመዘገቡት ድሎች በልመና የተገኙ ድሎች አይደሉም። ዉድ የኦሮሞ ልጆች በከፈሉት መስዋዕትነት የተገኙ ድሎች ናቸዉ። ዋንኛዉና ቀሪዉም ድል በኦሮሞ ልጆች ደምና አጥንት ብቻ የሚገኝ ይሆናል። ይህንን ሀቅ በመረዳት አዲሱ የኦሮሞ ተዉልድ በተለይም ከ 1991 በኋላ የተወለዱና በ QUBEE የተማሩ የቁቤ ትዉልድ ወጣቶቻችን የተጀመረዉን የነፃነት ትግል ለመጨረስና ቀሪዉን ድል ለመጎናፀፍ ከመቸዉም የበለጠ በቁርጠኝነት የተነሱ መሆናቸዉን እያሳዩ ነዉ። ስለዚህ የኦሮሞ ሕዝብ ከምድር ላይ እሰካልጠፉ ድረስ የነፃነት ትግሉ በየትኛዉም ሀይል መቆም አንደማይችል መረዳት አለባቸዉ።
በነገራችን ለይ ለኦሮሞ የነፃነት ትግል ፀር ለሆናችሁ ሀይሎች አንድ መርዶ ሳልነግራችሁ ፅሁፌን አልቛጭም። በናንተ ፍላጎትና ዓላማ እነድትጠፋ የሚትፈልጓት QUBEE ከጊዜ ወደ ጊዜ እያበበች መጥታ ይኸዉ ስለ ኦሮሞ ባሕልና ታሪክ የሚገልፁ በዚሁ ፊደላት የተፃፉ የ Afaan Oromoo መፃሕፍት ቁጥር እየበዙ መምጣታቸዉ ሲሆን፣ ባገኛሁት ኢንፎርሜሽን መሰረት ከቅርብ ጊዜ በፊት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ብቻ ቁጥራቸዉ ወደ አርባ ሦስት (43) የሚሆኑ በ QUBEE የተፃፉ መፃሕፍት ተመርቀዉ ገበያ ላይ መዋላቸዉን ነዉ። ታዲያ የነፃነት ትግሉም የመጨረሻዉን ድል እስከሚያስገኝ ድረስ እንዲሁ እያበበ እነደሚሄድ መረዳት አለባችሁ። ትግሉ ይቀጥላል። የመጨረሻዉ ድል የኦሮሞ ሕዝብ እንደሚሆን ጥርጥር የለዉም። እኛ ዛሬም ነገም ምንጊዜም ኦሮሞዎች ነን። አሮሚያ ለዘለዓለም ትኑር!!!!
Hordofaa Dhugaa: boontuus@gmail.com

No comments:

Post a Comment