ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ ታሰሩ
አንድነት የፊታችን እሁድ ለሚያደርገው ሰላማዊ ሰልፍ መቀስቀሱን; ኢሕአዴግ ማሰሩን ቀጥለዋል
25 september 2013 (Zehabesha) - የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት እና የአሁኑ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሊቀመንበር ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ መታሰራቸውን ብስራት ወልደሚካኤል ከአዲስ አበባ አዘገበ ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ መታሰራቸው የተገለጸው ዛሬ መስከረም 15 ቀን 2006 ዓ.ም. ሲሆን ዘ - ሐበሻ ወደ አንድነት ጽህፈት ቤት ደውላ "ዛሬ እስከ ጠዋት ድረስ ሥራ ላይ ነበሩ 'የሚል ምላሽ አግኝታ ነበር አሁን ይህን ዜና እየዘገብን ባለንበት ወቅት ወደ አዲስ አበባ የአንድነት አመራሮች ጋር ስንደውል ስልኮቻቸውን ያነሱ ሁለት የአንድነት አመራሮች የዶ / ር ነጋሶን መታሰር ለዘ -. ሐበሻ አረጋግጠዋል .
የፍኖተ ነፃነት ጋዜጠኛ ብስራት እንደዘገበው "አንድነት ፓርቲ አባላት በጉለሌ ክፍለ ከተማ መስከረም 19 ቀን 2005 ዓ.ም. በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለተጠራው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በሽሮ ሜዳ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ሳሉ መታሰራቸውን ተከትሎ የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ / ር ነጋሶ ያዘዝኩት እኔ ስለሆንኩ ልጆቹን ልቀቁ;. ከፈለጋችሁ እኔን ማሰር ትችላላችሁ በማለታቸው የጣቢያው ፖሊሶች ዶ / ሩ ነጋሶን ማሰራቸው ተረጋግጧል "
(የአንድነት አባላት በቅስቅሳ ላይ) ፎቶ ምንጭ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት
ፖሊሶች ዶ / ር ነጋሶን ከያዙበት ሽሮሜዳ ወደ ጉለሌ ፖሊስ መምሪያ በፖሊስ መኪና እና በበርካታ ፖሊሶች ታጅበው መወሰዳቸውን የዘገበው ብስራት በቅስቀሳ ላይ እያሉ የታሰሩትን የአንድነት ፓርቲ አባላትን ለማስፈታት ሄደው ዶ / ር ነጋሶ በምትካቸው በመታሰራቸው የተለቀቁት የአንድነት ፓርቲ አባላትም ቅስቀሳቸውን ቀጥለዋል.
በእሁድ መስከረም 19 ቀን 2005 ዓ.ም. በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ እያደረጉ የሚገኙ ከ 28 በላይ ሰዎችን ለማስፈታት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ያመሩት ዶ / ር ነጋሶ <ልጆቹ የፈጸሙት ህገ ወጥ ድርጊት የለም, ሲቀሰቅሱ የነበሩትም እውቅና የተሰጠውን ሰላማዊ ሰልፍ ነው. ቅስቀሳው ህገ ወጥ ነው የምትሉም ከሆነ እነርሱን የላኳቸው እኔ በመሆኔ እኔን ልታስሩኝ ትችላላችሁ "ማለታቸው ተዘግቧል.
ይህ ዜና እክሰተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ዶ / ር ነጋሶ ያልተፈቱ ሲሆን የፊታችን እሁድ ለሚደረገው ሰልፍ ቅስቀሳ ላይ ያሉት የአንድነት አባላት በቄራ አካባቢ ሲታሰሩ የሚቀሰቅሱበት መኪናም በፖሊስ ታግቷል.
No comments:
Post a Comment