(Deutsche Welle) — በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የሚገኙ ከአንደኛ እስከ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ተማሪዎች የአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን እና የመልካም አስተዳደር ጉድለትን በመቃወም ላይ ናቸው። በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙት ተማሪዎች ተቃዉሟቸዉን ካለፉት ሁለት ሳምንት ጀምሮ እያካሄዱ መሆኑ ታዉቋል።
ከኅዳር 9 ቀን 2008 ዓ,ም ጀምሮ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጃ የጋራ ማስተር ፕላን እና የመልካም አስተዳደር ጉድለትን በመጠቆም በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተማሪዎች ተቃዉሞ እያደረጉ ነዉ። ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸዉ በሰላም በሚካሄድ ትግል ዉስጥ ችግርን በይፋ መግለጽ በሕገ መንግስቱ የተደነገገ መብት መሆኑን እንደሚያምኑ የሚናገሩት ተማሪዎች የተጠቀሰዉ የማስተር ፕላን ልዩ ዞኑ ዉስጥ የሚገኙ ኗሪዎችን ከመሬታቸዉ እንደሚያፈናቅል ያም አግባብ እንዳልሆነ ይናገራሉ። ከዚህም ሌላ ከአደስ አበባ ከተማ የሚወጡ ፈሳሾች ለሰዉም ሆነ ለእንስሳዎች ጠንቅ በመሆኑ መፍትሄ እንዲፈለግ ተቃዉሞ ማሰማታቸዉን ያስረዳሉ። በተጨማሪም የመልካም አስተዳደር እጥረት ያመጣዉ ነዉ ያሉት በግንጭ የሚገኘዉን የጭልሞ ጫካ ለግለሰቦች መንግስት ሸጧል በሚልም ተማሪዎቹ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ተማሪዎች ተቃዉሟቸዉን አሰምተዋል።
በተቃዉሞዉ ወቅትም ቁጥራቸዉ ብዙ የሆኑት ተማሪዎች እንደታሰሩ፣ በፖሊስ ሃይልም ድብደባም የተጎዱ መኖራቸዉን ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የጠየቁ እማኝ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። <<በአምቦ የመሰናዶ ትምህርት ቤት እና በድሬ እንጭኒ ተማሪዎች ለሰለማዊ ሰልፍ ወጥተዉ ነበር። እሱንም ተከትሎ የኦሮሚያ ፖሊስ ተማሪዎቹን ማሰር ጀመረ። ሕዳር 14 ዘጠኝ ተማሪዎች ታስረዋል፣ ትላንትም ብዛታቸዉን ባላዉቀዉም ወደ አምስት ተማርዎች መታሠራቸዉን ሰምቼ ነበር። በተጨማሪ እሄን እስር አምልጠዉ ወደ ፊንፊኔ የሸሹ ተማሪዎች እንዳሉ ሰምቼ ነበር።
ሌላዉ ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉ የ89 አመት አዛዉንት በበኩላቸዉ ሱሉልታ አካባቢ ባለፈዉ ሳምንት ጀምሮ 600 ቤተሰብ ይኖርበት በነበረ ቦታ ላይ መንግስት ኢንዱትሪ ለመገንባት በመፈለጉ ካሳ ሳይሰጥ ኗሪዎቹን እንዳስነሳ ይናገራሉ። ለዚህም ወደ ኦሮሚያ ክልል መንግስት ድረስ ሄደዉ ቢጠይቁም መልስ አለማግኘታቸዉን እንደዉም እዚያ የሚገኙ የመንግስት ካቢኔዎች በእስር እንዳሰፈሯሯቸዉ ይናገራሉ። አዛዉንቱ አክለዉም፤ <<የተወለድንበትን ቦታ ትተን የት ነዉ የምንሄደዉ? ልጆች አሉን፣ እንስሶዎች አሉን፣ የት ነዉ የምንሄደዉ? አዉሬ ይበላናል፤ ማንስ ያስጠጋናል።
ይህን በሚመለከት ምላሽ ለማግኘት ከፌዴራልም ሆነ ከኦሮሚያ መንግስት የሚመለከታቸዉን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነዉ ሙከራ አልተሳካም።
መርጋ ዮናስ
ሸዋዬ ለገሰ
ኦሮሚያ ውስጥ እየታየ ላለው የተማሪዎች ተቃውሞና መዘዝ ተጠያቂው መንግሥት እንደሆነ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ – ኦፌኮ ክሥ አሰምቷል፡፡
አዲስ አበባ — (VOA News) — የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ – ኦፌኮ በአሁኑ ጊዜ የሃገሪቱ አንድነት ያለው “አጠያያቂ ሁኔታ ላይ ነው” ብሏል፡፡
እስከአሁን ለተፈጠሩ ችግሮችና ወደፊትም ሊከተሉ ለሚችሉ አደጋዎች ተጠያቂው “ፌደራል ሥርዓቱን እየናደ ነው” ያለው “መንግሥት ነው” ሲልም ከስሷል፡፡
“ኦሮሞዎችን የማሠር ዘመቻ ተጀምሯል” የሚለው ኦፌኮ እንቅስቃሴው እንዲቆም በመጠየቅ ባለአሥር ነጥብ መግለጫ አውጥቷል፡፡
No comments:
Post a Comment