እኤአ በ1991 ስልጣን የተቆናጠጠው አረመኔያዊው የወያኔ ስርዓት በ23 አመታት ውስጥ በዜጎች ላይ ይህ ነው የማይባል ኢ ሰብዓዊ ድርጊት በመፈፀምና የህዝቦች ቀንደኛ ጠላት በመሆን የስልጣን ዘመኑን በማርዘም ላይ ይገኛል:: በተለይም ከጊዜ ወደጊዜ በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየከፋ የመጣው የጭካኔ ዘመቻ ከየትኛውም ጊዜ በላይ በመባባስ ላይ ይገኛል::
የስርዓቱ ባለስልጣናት የኦነግ አባል የሆኑትን ብቻ ሳይሆን ያልደገፋቸውን ያላጨበጨበላቸውን የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑትን ማሰር፣ ማፈን፣ አፍኖም ማሰቃየት፤ከዚያም ደብዛቸውን በማጥፋት መግደል፤ ሃብት ንብረታቸውን መውረስ፤ እነርሱን አስሮ ቤተሰቦቻቸውን ከ ህብረተሰቡ እንዲገለሉና ከአገር እንዲሰደዱ በማድረግ ከፍተኛ የሆነ ለሞራል ውድቀትና ድቀት እየዳረጉ እንደሚገኝ ለማንም ግልፅና የሚታወቅ ነው፡፡ በተለይ ፀረ ሽብር በሚል ሽፋን አሻንጉሊቱ ፓርላማ ባወጣው አዋጅ ቁጥር 652/2001 ኦነግንና አንዳንድ የነፃነት ታጋይ ድርጅቶችን አሸባሪ ብሎ በመፈረጅ አባል ናቸው ተብለው ከሚጠረጠሩ ግን ዓባል መሆናቸው በይፋና በግልጽ ከማይታወቁ ሰዎች ጋር ሰላምታ መለዋወጥ፤ አብሮ መሄድ፤ ሻይ ቡና መገባበዝ፤ መመገብ ሰላምታ ያደረጉ ሰዎችንም የአሸባሪነት ሰለባ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡ በፀረ ሽብር ሕጉ ላይ ሌላ ጊዜ በሰፊው እመለስበታለሁ፡፡
ዛሬ ማውሳት የፈለኩት ግን ከላይ በጠቀስኩት ዓይነት እንደዋዛ ከቤት ወጥቶ ወደቤቱም ያልተመለሰውንና የተረሳው የኦሮሞ ተወላጅ ይሆናል፡፡ ስሙ አቶ አብደላ ፈቁ ይባላል፡፡ የትውልዱ ስፍራም አርሲ ክ/ሃገር ነው፡፡ ከወ/ሮ መኮ አብደላ ጋር ከተጋቡ በኋላ የእህል ውሃ ጉዳይ ሆኖ በቀድሞው አጠራር ቦረና ዞን አሁን ጉጂ ዞን ዋደራ ወረዳ ኑሯቸውን መስርተውና አደራጅተው ይኖሩ ጀመር፡፡ ዋደራ ከ አዲስ አበባ በስተ ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ 525 ኪ/ሜ ነው፡፡ አየሯም ወይና ደጋ ሲሆን የገጠሩም ሆነ የከተማው ነዋሪ የሚተዳደረው ከብት በማርባት ነው፡፡ ከበስተ ምዕራብ የዳዋ ወንዝ ገባሪ የሆነው አዋጣ ወንዝ በስተ ምስራቅ ደግሞ ከባሌ ክ/ሃገር በሚለያት የገናሌ ወንዝ ትዋሰናለች፡፡ኑሯቸውን በዚችው ከተማ እንዳደረጉ ልጅ መውለድ ጀምረው በእስራ ቁጥጥር ስር እስከዋለበት ዓመትም 7 ልጆችን አፍርተዋል፡፡ አቶ አብደላ የተዋጣለትና የተሳካለት ነጋዴ ሆነ፡፡በከተማው የገባያ አንብርት ትልቅ ሱቅ ከፈተ፡፡ ከአሰብ ጨው እያስጫነ እዚያ ድረስ ወስዶ በማከፋፈል የታወቀ ነበር፡፡ በዚህ ሁሉ ሂደት ውስጥ ግን ከማህ በረ ሰቡ ጋር የነበረው መልካም ግንኙነት በእድሜ የሚበልጡት ሰዎች እንኳ ስሙን በነጠላ የሚጠራው አልነበረም፡፡ “ጋሼ’ ን ጨምረው “ጋሽ አብደላ’ ነበር የሚሉት፡፡ በግል ችግሩ ምክንያት አቶ አብደላ ዘንድ የሄደ ችግሩ ሳይፈታ አይመለስም ነበር፡፡ ከሱቅ እቃ ፈልጎ የመጣም ቢሆን የፈለገውን እቃ፤ የገንዘብ ብደር የፈለገም ቢሆን የፈለገውን ያህል ገንዘብ ሳይቀበል የመለሳል ማለት ዘበት ነው፡፡ የታመመ መታከሚያ ቢያጣ እርሱ ከሰማ ህክምና አግኝቶ በጤና እንደሚሰነብት ማንም አይጠራጠርም፡፡
በዚሁ ደግነትና ቸርነቱ ተወዳጅነቱ እየጨመረ የሱቅ ንግዱ እየተቀዛቀዘ ሱቁም እየከሰረ መጣ፡፡ ይህን የተመለከተ የመክሰሩ ምክንያት በብድርና በዱቤ የወሰዱትን ገንዘብ ባለመመለሳቸው እርሱም አምጡ ብሎ ባለማስጨነቁ እንደሆነ በከተማዋ በሰፊው ይወራ ነበር፡፡ የሆነው ሆኖ ቀስ በቀስም ሱቁ ተዘጋ፡፡ አቶ አብደላም ከብት እየገዛ እዚያው እያተረፈ መሸጥና መደለል ጀመረ፡፡ የኑሮ ደረጃው ዝቅ ቢልም በህዝቡ ዘንድ የነበረው አክብሮት ቅንጣት ታክል አልቀነሰም፡፡ ሀዘኔታውና ፍቅሩ ጨመረ አንጂ፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላም እኤአ 1991 ከተደረገው የመንግስት ለውጥ በኋላ በራሱ ህብረተሰቡን በማረጋጋቱ አንዱ ባንዱ እንዳይነሳ በማድረጉ ሂደት ያደረገው አስተዋፅኦ ቀላል አልነበረም፡፡በዚሁ ዓመት በተቋቋመው የሰላምና መረጋጋት ኮሚቴ ውስጥ ያደረገው አስተዋፅኦ ቀላል አልነበረም፡፡ ወዲያው በተደረገው አዲሱ የቀበሌ አደረጃጀትም ቀበሌ ከተማ አስተዳደር በሊቀመንበርነት ተመረጠ፡፡ ግሩም ድንቅ ነበር እያንዳንዱ ችግሩ ይፈታ ነበር፡፡ መታወቂያ ለማግኘት፤መሸኛ፣የቀበሌ ቤትና ማንኛውም ድጋፍ ማመልከቻ ላይ መፈረምና ትዕዛዝ ለማስፃፍ አብደላን ቢሮ ውስጥ መቀመጫው ላይ ተቀምጦ ማግኘት ግድ አልነበረም፡፡ ለልዩ ልዩ ጉዳይ በከተማው ሲዘዋወር፤ በእርሻ ስፍራ ፤ለቅሶ ቤት፤ቀብር ላይም ቢሆን፤ ገበያ ውስጥ ብቻ የትም ቦታ “ጋሽ አብደ ብሎ ለጠራው ምን ችግር ? ‘ ነበር የሚለው፡፡ ከዚያ ጉዳዩም በዚያው አለቀለት፡፡ የሚፈልገውም ተፈፀመለት ማለት ነው፡፡ በርሱ የአስተዳደር ዘመን ተጣልቶ ለክስ ማህበራዊ ፍርድ ቤት የሚሄድ አልነበረም፡፡ ፖሊስ ጣቢያም ቢሆን፡፡ ሊከስ የሄደው ሲመለስ አግኝተው ቢጠይቁት ” ጋሽ አብደላ ትተህ ተመለስ አለኝ ፡፡ ‘ ነው የሚለን፡፡ ከጥቂ ወራት ቆይታ በኋላ የወያኔ ካድሬዎች ጨካኝ ወታደሮቻቸውን በማሰማራት በከተማው የቤት ለቤት የመሳሪያ ፍተሻ መሳሪያ አለው ታጥቋል ብለው የጠረጠሩትን ሁሉ ሰብስበው በከተማው እምብርት ከሚገኘው የፖሊስ ጣቢያ እስር ቤቱ ቢሞላ እዚያው ግቢ ከሚገኘው ከሳር ክዳኑ ከፈረሰበት መዝናኛ ክበብ ውስጥ አጉረው በላያቸው ዝናብ እየዘነበ አድረው ውለው በሌላኛው ቀን ምሽት እያንዳንዱን እያወጡ የቻይና ካራቲስቶች ትርኢት በሚያሳዩበት ኪንዶ በሚባል በሰንሰለቱ ጫፍና ጫፍ ላይ የእንጨት መያዣ ባለው መሳርያ እያነቁ ሲያሰቃዩ ለፀትታ ቁጥጥር ከሚዞርበት ድንገት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ገብቶ ያለውን የህዝብ ስቃይ አይቶ በመቃወሙ እርሱንም አስፈራርተው እንዲሄድ ቢያደርጉት ፍንክች አላላም፡፡
ለህዝብና ከህዝብ ጎን የቆመ በመሆኑ ቤቱ ሳይገባ ያድራል፡፡ በወቅቱ ምንም ማድረግ የማይችል መሆኑን ባወቀ ጊዜ ስቀስቅ ብሎ ያለቅሳል፡፡ አምባገነኖቹ ያሰሯቸውን ሰዎች ማሰቃየታቸውን ቀጥለዋል፡፡ “በሉ ! . . . . በሉ! ይህን የማሰቃያ ድርጊት ማቆም ካልቻላቻሁ እኔንም ከነርሱ ጋር ቀላቅላችሁ በነርሱ የምታደርሱትን ስቃይ ለኔም አካፍሉኝ፡፡ ማን ምን እንደሆነ እኛን ብትጠይቁን እንነግራችኋለን ማንም በቂም በቀልና ጥላቻ ላይ ተመስርቶ በሰጣችሁ ጥቆማ ምንም የማያውቁና ከምኑም የሌሉ ሰዎችን እንዲህ ሲሆኑ ከምመለከት ዛሬ ሞቴን እመርጣለሁ . . . ‘ በማለት ያለማቋጥ ሲናገር ተጋዳላይ የወያኔ ወታደርና ካድሬዎች አንቀውና ገፈታትረው ቀላቀሉት፡፡ ለመሆኑ እራሱን እንዲህ ለሌሎች ቤዛ አድርጎ የተገኘ ማነው ? ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለምን ? በኋላም ቆይተውም ማንነቱን አጣርተው ሊቀመንበር መሆኑን ሲረዱ ግማሹ ” ይሄ ለራሱ ሽግር ዓለበት. . . እ . . . ዋ. . . ይ ! ቦሉት ! ፡፡ ‘ ብለው እንዳዘዙ እርስ በርስ ተመካክረውም አሰሩት፡፡ ሊነጋጋ ሲልም አውጥተው ቢሮም በማስገባት አግባብተው ሰዎቹንም እንደሚለቋቸው ቃል ገብተውለት የፖሊስ ጣቢያውን ለቆ እንዲወጣ አስጠነቀቁት፡፡ አውለው አሳድረውም ቢሆን ሁሉም ሰዎች ከእስራት ተፈቱ፡፡ አብደላ ስራውን ቀጥለሏል፡፡ ከጥቂት ወራት በኋላ የሆነው ግን በራሱ ህልውና የመጣ መሆኑ አልታወቀውም፡፡ አብደላ ምንም በማይታወቅ ምክንያት ታሰረ፡፡ በፖሊስ ጣቢያው የሚርመሰመሰው ህዝብ ልክ አጣ፡፡ የእድሜና የፆታ ገደብ አልነበረውም፡፡ አብዛኛው ሰው ጠዋት ፣ቀንና ማታ ሄዶ የማይጠይቅ ቁርስ ምሳ እራት በግል በቡድን የፖሊስ ጣቢያውን በረንዳ በዳንቴልና በፌስታል የታሰሩ የምሳ እቃዎች ተጨናነቁ፡፡በተለያየ ወነወጀል ተጠርጥረው የታሰሩ እስረኞችም መመገብ ታክቷቸው ከሃብታም ቤት ፤ከድሃ ቤት የመጣ፤የስጋ፣ የሽሮ እያሉ ማማረጥ ቀጠሉ፡፡በሻይ የተሞሉ ፔርሙዞችም እንዲሁ ሰልፋቸውን ከሩቅ ላየው የተለየ ነገር ነው የሚመስለው፡፡ ክሽን ያለ ወጥ ሰርታ ሳህን ቋጥራ ማምጣት ያቃጣት ሴት ሻይ አፍልታ በፔርሙዝ ከአንባሻ ጋር ማምጣት አያቅታትም፡፡ አቶ አብደላን ለመጠየቅ የሚመጣን ሰው የእስረኛ መጠየቂያ ሰዓት አይደለም ቢባል እንኳ ህዝቡን ማስቆም ስላልተቻለ ከጭለማው ክፍል አውጥተው ከአዛዡ በረንዳ ላይ ፍራሽ አስነጥፈውት እዚያ ላይ አረፍ ብሎ እርሱን ጥየቃ የሄደን ህዝብ ማስተናገድ ቀጠለ፡፡ በምን ምክንያት ታሰርክ ? ‘ የሚለውን የህዝብ ጥያቄ እርሱንም ግራ እንደገባውና እንደማያውቅ ነበር ደጋግሞ የሚናገረው፡፡ ህዝቡ ግን የራሱን መላ ምት ነበር የሚያቀርበው፡፡ ” እነዚህ አጭበርባሪዎች አዘናግተውት ፤ አታለውት ፤ የዋህነቱን ተጠቅመው አስፈርመውት የመንግስት ገንዘብ አጉድለውበት ነው፤ ከሆነ ደግሞ ይንገሩንና እናወጣለት ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ ለጋሽ አብደላ ያልሆነ ገንዘብ ደግሞ . . . ‘ እያለ ወስጥ ውስጡን ሲያወራ ምርመራ ተካሄደበት የሚል ወሬ ተሰማ፡፡ ምክንያቱን ለወቅ ጆሮ በጆሮ የሆነቸው ከተማ ጉዱን ሰማች፡፡ “አብደላ የኦነግ ዓባል መሆኑ ተረጋገጠ፡፡ ከሱቁ የእጅ ባትሪ ቀፎ ፤ ባትሪ ድንጋይ ፤ ስኳር፣ የተፈጬ ልዩ ልዩ እህሎች ዱቄት በማዘጋጀት ከዋደራ በስተ ምስራቅ አቅጣጫ ባለውና አስከ ደሎመና በሚዘልቀው ጥቅጥቅ ደን ውስጥ መሽጎ በመላዋ ባሌና አርሲ ከሐረረጌ እስከ ቦረና ጫፍ ተስፋፍቶ የነበረውን የትጥቅ ትግል በከተማ መሽጎ ድጋፍ እየሰጠ ኖሯል አሁን ግን በቃ፡፡. . . ‘ ከቀናት ቆይታ በኋላ ለጥየቃ ምናምን ይዘው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ይሄዱ የነበሩ ሰዎችን “ለምርመራ ወደ ዞን ነገሌ ቦረና ተወሰደ’ ተባለ፡፡ አባባሉ ሰውን እጅግ ያስደነገጠ ነበር፡፡ ከሳምታት በኋላ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ዋደራ አመጡት፡፡ ህዝብ ግልብጥ ብሎ ለጥየቃ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄደ፡፡ ምላሹ ግን አንገት ያስደፋ ነበር፡፡ ”
ከማንም ጋር መገናኘትም መነጋገርም አይፈቀድለትም ‘ ተባለ፡፡ አንዳንድ የቅርቡ የሆኑ ሰዎች በሚስጥር ገብተው የጎበኙት ሲናገሩ ግን አቶ አብደላ የነበረበት ሁኔታ ለቅንነቱና ደግነቱ በሚገባው ሁኔታ ላይ አልነበረም፡፡ቅስሙ ተሰብሯል ፊቱም ተጎሳቁሎ እና ገርጥቶ ተስፋ መቁረጥ ይነበብበታል፡፡ እጅና እግሩም እንደልብ አይታዘዙለትም፡፡ ክፉኛ ተደብድቧል ሳይሆን በደንብ ተቀጥቅጧል ማለቱ ይቀላል፡፡ ብረቱ ሰው ስለነበረ ነው በርትቶ የታየው፡፡ በጣም የሚገርመው ግን ቤቱ፣ቢሮው፣ ሱቁ ቢበረበርም ምንም መረጃ አለመገኘቱ ነው፡፡ ቀጣዩ የነጌሌ ቦረናው ጉዞ እርሱን ቤተሰቡንና ህዝቡን ዳግም እንደማያገናኛቸው ሲረዳ ፊቱ ቅጭም ብሎ ልቡ ፍርጥ ልትል ምንም አይቀረው፡፡ከንፈሩን ብቻ ይነክሳል፡፡ ሄዶ የማይሰለች ቆሞ የማይደክምው እግሩ እንደልባቸው አይቆሙም፡፡ ወደ ነገሌ ቦረናም ተወሰደ ፡፡ ባለቤቱ ፣ልጆቹ አቅም ያለው ና የቅርብ ጓደኞቹ 60 ውን ኪ/ሜ እየተመላለሱ ጠየቁት፡፡ከወራት በኋላ ግን ሲሄዱ መጠየቅ አትችሉም፡፡’ ተባሉ አጥብቆ ለጠየቀ ደግሞ “ወደ ሌላ እስር ቤት ተዛውሯል፡፡’ ተባሉ፡፡ ወዳጅ ዘመድ ባልተ ቤቱ ዝዋይንና የመሳሰሉትን እስር ቤቶች አካለው አካለው ተስፋ ቆርጠው ተዉት፡፡ደብዛውም ጠፋ፡፡ሞቶ ሞተ አልተባለም፡፡ኖሮ ደግሞ አልታየም፡፡ በቅርቡ በመሃል አዲስ አበባ ከ6ኪሎ ፈረንሳይ ያለው አስፓልት መንገድ ሲሰራ ጃን ሜዳን አለፍ እንዳለ ከሚገኘው ወታደራዊ ካምፕ ግቢ ከነበረው ተቀንሶ ለመንገድ የተተወው መሬት በኤክስካቤተር ሲታረስ በደብረ ብርሃን ብርድ ልብስ ፋብሪካ ምርት በሆነው ከ24 ዓመት ወዲህ እንደሆነው ከተገመተውና ከተቀበረበት የወጣው የ6 ሰዎች አፅም የሚያሳየንም ብዙ አብደላዎች አመለካከታቸው የተለየበመሆኑ ብቻ ከቤትና ቤተሰቦቻቸው ተለይተው እንዲህ እንደዋዛ ተገድለው የትም ይጣላሉ፡፡ አይ ኢትዮጵያ፡፡
ሰላም፡፡
No comments:
Post a Comment